ጠቅላላ የ አጃከስ ሳሙና ዝርዝር መረጃ በሰአት ከ800-1000 ማምረት የሚችል ሲሆን ማሽኑ ሁለት ክፍሎች አሉት እነዚህም ፕሮደር እና ሚክሰር ናቸው፡፡ ይህ ማሽን 3 ፌዝ (phase) ቆጣሪ (ሀይል) ወይም 15kw (15 ኪሎዋት) የሚጠቀም ማሽን ነው፡፡ ስራውን ለመስራት 50 ካሬ ቦታ በላይ ያስፈልጋል ማሽኑን ለመግዛት 200 ሺህ ብር ያስፈልጋል ምርቱን ለመጀመር ጠቅላላ የጥሬ እቃ ዋጋ 50 ሺህ ብር ያስፈልጋል ድርጅታችን ይህንን ማሽን ሲያቀርብ ጥሬ እቃ ከአስመጪዎች ጋር ያገናኛል እንዲሁም ድርጅቱ በሚያቀርበው ማሽን ሙሉ ስልጠና እና ማሽኑ ለሚያጋጥመው ችግር የአንድ አመት ዋስትና ይሠጣል፡፡የአጃክስ ምርት ኢትዮጵያ በመላው ሀገር ተጠቃሚው እጅግ በጣም ሰፊ ስለሆነ ምርቱን ለመሸጥ እና ገቢያ ውስጥ ለመግባት እጅግ በጣም ቀላል ያደርገዋል፡፡ የአጃክስ ሳሙና ትርፋማነት እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡ አንድ የአጃክስ ሳሙና ለማምረት አምስት (5) የተለያዩ ኬሚካሎች ያስፈልጉታል፡፡ እነዚህም ላብሳ, ሲልኬት, ሶዳአሽ, ሶዲየም ሲልኬት እና ዶሎማይት ናቸው፡፡ እነዚህን ኬሚካሎች ለመቀላቀል ወይም ለማዋሀድ በቂ የሆነ ስልጠና ከድርጅታችን በመውሰድ የአጃክስ ሳሙና መስራት ይቻላል፡፡ የአንድ አጃክስ ሳሙና ክብደት ትንሹ አንድ መቶ ግራም (100) ሲሆን ትልቁ ደግሞ ሁለት መቶ ግራም ነው፡፡ የ100 ግራም አጃክስ ሳሙናን ለማምረት ጠቅላላ ጥሬ ዋጋ 1 ብር ከዘጠና ሳንቲም ሲሆን ትልቁን አጃክስ 200 ግራም አጃክስ ሳሙና ለመስራት ደግሞ 3 ብር ከሰማንያ ሳንቲም ይጨርሳል፡፡ አሁን ባለው የአጃክስ ሳሙና ዋጋ ትንሹ ስድስት ብር (6 ብር) ትልቁ 10 ብር ነው፡፡ ስለዚህ አንድ አጃክስ ማምረቻ ባለቤት ትንሹን አጃክስ በትንሹ 3-4.50ሳ ከአከፋፋይ ወይም ትልቁን አጃክስ ከ5-6.50ሳ ለአከፋፋይ ቢያስረክብ ከ1 ብር እስከ 2.50 ሳንቲም ትርፍ ማግኘት ይችላል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው ይህ የአጃክስ ማሽን በቀን ከ6400-8000 ፍሬ አጃክስ ማምረት አቅም ሲኖረው የኤሌክትሪክ ፍጆታው በወር 1800 ብር ይደርሳል፡፡ እንዲሁም 60 ፍሬ አጃክስ የሚይዝ ካርቶን በ6.50 ሣንቲም ወጪ ስለሆነ ይህንን ማሽን በመግዛት ወደ ስኬታማ ቢዝነስ መቀላቀል ይችላሉ፡፡ ከተገለፀው ውጭ ብቻ ጥያቄዎች ካልዎት በድርጅቱ ስልክ ይደውሉ፡፡እነዚህ ኬሚካሎች አብዛኛቹ 90 ፐርሰንቱ በሀገር ውስጥ በበርካታ ቦታዎች የሚገኙ ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ ከውጭ ሀገር የሚገኙ ናቸው እነዚህን ኬሚካሎች ለማግኘት ከታች ባሉት ስልኮች መጠቀም ይችላሉ፡፡
Ещё видео!