#ethiopia
|| ኢትዮጵያ|| ሙሉ ግጥም
አብዛኛው ሃሳብ የተወሰደው ከኛ ሳሙኤል 17:45 ነው
ቢመክት የቱ ጉልበቴ
የተናቀው እስካባቴ(እስከ ዘሬ)
ደሞ ላንተ የሚለኝን
የናቀኝን
ያ ፈረሱን ጦሩን ታምኖ (ሃብቱን ተማምኖ)
ባገሬ ላይ ክንዱ ገኖ
ቀንና ሌት ቢያስፈራራኝ
እንዲያው ምን አለኝ....(ስለ ግብፅ እና በላዩ ስለሚሰራው መንፈስ)
ታሪኬን ሊቀብረው ትልቅጉድጓድ ምሷል
ልክ ነው እንዳለው ጋሻ ጦሩን ለብሷል
ግን ኪዳን የሌለው ይሄ ሸለፈታም
እንኳን እኔን ቀርቶ ጥላዬን አይመታም (ይሄ የጎሊያድ እና የዳዊት ታሪክ ነው)
እስቲ ይድረስ ከደጄ ይሞክረው ደርሶ
በኋላ ያየዋል ሃይሉ በኔ ብሶ
ምን ኖሮት ነው ይላል አረ ማንን ቢያምነው
ሄዳችሁ ንገሩት ነገሩ ወዲህ ነው....
ኪዳን ነው ሚያኖረኝ
ኪዳን ነው ተስፋዬ
ቀና ያደረገኝ
የቱ ትከሻዬ!(2) (ስለ ኢትዬጵያ ነው)
መቶ ይመልከተው ቤት ቀዬውን እግዚያብሄርን ብሎ የኖረውን
ጉልበቱ አምላኩን ያደረገ አዳኝ ከሰማይ ነው የሚለውን
እንደስራኤል እንደከበቧቱ ያዝኩህ ብሎ ጠላቱ ቢመኘኝም
አባቱ የኢትዮጵያም አምላክ ነው እኔን አይደል ዘሬን አያገኝም (ለክፉ መንፈስ)
ኪዳን ነው ሚያኖረኝ ኪዳን ነው
ኪዳን ነው ተስፋዬ
ቀና ያደረገኝ የቱ ጠመንጃዬ(2) ስለ ኢትዮጵያ!"(ስለ እኔ)
(1) ተራራው ዙሪያውን አይኑንን እያቅላላ
ከጀርባው ጠላቱ ክፋቱን ሲሞላ (ክፉ መንፈስ)
ነገ ወደ ሰማይ መዝርጋቱን አይቶ
ቀስተ ደመናው ላይ የሞት አዋጅ ወቶ ስለ (በክፉ መንፈስ)
ቢዚህ ቢኬድ በዚያ በኩል ኪዳን አልፎ ሚደርስ ማነው
ጉልበተኛም አይገዛትም "ያገሬ"እጅ ወደ ላይ ነው
ሊቅ አውንቱ ሚመኩበት ሰው የሰራው ቅጥር ባይኖር
የሚያጥፋ "ኪዳን" አለን ለዘላለም ፀንቶ ሚኖር!!
አይዞሽ "ኢትዮጵያዬ"አይዞሽ ኪዳን አለም!!
ሰላምሽ ወዲህ ነው አይዞሽ እልፍ "ጦር"አይደለም
አይዞሽ "ኢትዮጵያዬ" አይዞሽ ከዚም ከዚያም አትፈልጊ
"አዳኝሽ" ከላይ ነው አይዞሽ እጆችሽን ዘርጊ!!
አሁን ስላለው የኢተዮጵያ ችግር አና ስለ ኢትዮጵያ ድህነት""
ጥለህ ሂድ ይለኛል ጥለህ ሂድ ይለኛል የት ልሂድ ካገሬ
ፈተናው ቢበዛ ድህነት ቢይዘው ባይቀና መንደሬ
የሄደውም ይምጣ መንገድ የጀመረ አልነቃነቅም!!
ቀኔ በምድሬ ነው ቀኔ በኢትዮጵያ ነው ሃገሬን አለቅም
አለቅም ኪዳኔን አለቅም
ተስፋዬ ቢቀርብም ቢርቅም
አለቅም ኢትዮጲያን አለቅም
"ቃል አለኝ" ሌላውን አላውቅም!!
እንዲ እንዲያ እያለ ክፋት እያብላላ
በጎሳና በዘር ትውልዴን የበላ
ሃይለኛ ነኝ ብሎ አለም ሁሉ ቢያምነው ( ክፉ ዲያቢሎስን)
እመነኝ ያገር ልጅ ድሉ የእግዚያብሄር ነው
ቢዚህ ቢኬድ በዚያ በኩል ኪዳን አልፎ ሚደርስ ማነው
ጉልበተኛም አይገዛትም "ያገሬ"እጅ ወደ ላይ ነው
ሊቅ አውንቱ ሚመኩበት ሰው የሰራው ቅጥር ባይኖር
የሚያጥፋ "ኪዳን" አለን ለዘላለም ፀንቶ ሚኖር!!
አይዞሽ "ኢትዮጵያዬ"አይዞሽ ኪዳን አለም!!
ሰላምሽ ወዲህ ነው አይዞሽ እልፍ "ጦር"አይደለም
አይዞሽ "ኢትዮጵያዬ" አይዞሽ ከዚም ከዚያም አትፈልጊ
"አዳኝሽ" ከላይ ነው አይዞሽ እጆችሽን ዘርጊ!!
አሁን ስላለው የኢተዮጵያ ችግር አና ስለ ኢትዮጵያ ድህነት""
ጥለህ ሂድ ይለኛል ጥለህ ሂድ ይለኛል የት ልሂድ ካገሬ
ፈተናው ቢበዛ ድህነት ቢይዘው ባይቀና መንደሬ
የሄደውም ይምጣ መንገድ የጀመረ አልነቃነቅም!!
ቀኔ በምድሬ ነው ቀኔ በኢትዮጵያ ነው ሃገሬን አለቅም
አለቅም ኪዳኔን አለቅም
ተስፋዬ ቢቀርብም ቢርቅም
አለቅም ኢትዮጲያን አለቅም
"ቃል አለኝ" ሌላውን አላውቅም!!
Ещё видео!