ጊዜ የማይገድባቸው ድንቅ የታደሰ እሸቴ ዝማሬዎች ከነሙሉ ግጥሞቻቸው
የተለያዩ መንፈሳዊ ቪዲዮዎች እንዲደስሮ ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ አባሎቻችን ይሁኑ
የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ
የእግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ
ደካሞችንም ማገዙ
በጀርባው አዝሎ መሸከሙ
ከሐጥያት ማንፃት በደሙ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ
እኔስ አይቻለው ፍቅሩን
ከፋንድያ ላይ ማንሳቱን
ዛሬ ሰው ሆኜ እዘምራለው
ለዚህ ክብር በቅቻለው
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ
እጅግ ተንቄ በሰው ልጅ
ተጥዬ ነበር በአመድ
ግን ጌታ ኢየሱስ ፈልጎኝ
ከሐጥያት መዐት ውስጥ አወጣኝ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ
አይገርማችሁም ወይ ወገኖች
የልኡል አምላክ ባሪያዎች
ተነሱ ዘምሩ ለጌታ
እጅግ ብዙ ነው ውለታው
የእግዚአብሔር ምህረቱ ብዙ
ደካሞችንም ማገዙ
በጀርባው አዝሎ መሸከሙ
ከሐጥያት ማንፃት በደሙ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ጌታ ሆይ
ለዚህ ያደረስከኝ አንተ አይደለህም ወይ
tadesse eshete amazing gospel music, classic music
subscribe our channel for more videos
Ещё видео!