በስመዓብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡የማይሠለች ምስጋና የተወደደው ውዳሴ ሁሉ ከሁሉም በላይ ላንተ ይሁን፡፡
አይሠለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚዓብሄር በዘመኔ
ቸርነትና ፍቅሩን ያላረቀ ከባሪያው
በለመለመው ስፍራ በጎቹን የሚያሠማራው
ታላቅ ነው የእኛ ንጉስ ታላቅ ነው የእኛ ጌታ
መፅሐፉን የዘረጋ መኅተሙን የፈታ
አይሠለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚዓብሄር በዘመኔ
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና እንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በሕይወት አቁሞኛል
አልችልም የዕርሱን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ውለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት
አይሠለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚዓብሄር በዘመኔ
የአንተ ክንድ የማይንደው ተራራ ጋራ የለም
ወጥቻለሁ ከጥልቁ ታላቅ ነህ ዘለዓለም
የተከፈተ ደጃፍ ሠጥተኸኛል በፊቴ
ተመስገን ክበርልኝ ንገስልኝ አባቴ
አይሠለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚዓብሄር በዘመኔ
ለይተህ የጠራሐኝ ያበዛህልኝ ፀጋ
ትዝታዬ ነህ ጌታ ሲመሽ እና ሲነጋ
ወዳጅ እና ዘመዴ ብዬ ስጠራህ ልኑር
እየሱስ የእግዚዓብሄር ልጅ ለወጠኝ የአንተ ፍቅር
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና እንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በሕይወት አቁሞኛል
አልችልም የዕርሱን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ውለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት
አይሠለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚዓብሄር በዘመኔ
Ещё видео!