Dawit Getachew
ዳዊት ጌታቸው
Ante kibre neh
አንተ ክብሬ ነህ
Album - Amnhalew
ይሄ ቢሆንልኝ ብዪ የምመኘው
ህልሜ እውን ሆኖ መች ነው የማየው
ብዪ የማስበው የማልመው ነገር
ተሰጥቶኛል አንተን ያገኘሁኝ ቀን
ተራራ አልወጣሁ ወይ አልወረድኩኝ
ግን እንዲሁ በፀጋህ ስለወደድከኝ
ከምለምነው እና ከማስበው በላይ
ቤት ሰርተህልኛል በሰማይ
አንተ ክብሬ ነህ አንተ ጥበቤ
ቅድስናዪ የሱስ ቤዛዪ
ምን አለኝ የምሻው ከእንግዲህ
ሁሉም ተሰጥቶኛል በስምህ
ፍቅርህን እያየሁ ሁሌ አመልክሀለሁ
የእግዚአብሔር ልጅ ወድሃለሁ
አሁን ያንተ የሆነው ሁሉ የኔ ነው
ፍለጋ አልወጣም ማዶ ማዶ እያየሁ
የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠኸኝ
ከአንተ የተነሳ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ
የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠኸኝ
ካንተ የተነሳ የንጉስ ልጅ ነኝ
ነጻ ወጥቻለሁ ከሀጥያት አበሳ
ባርነቴ ቀርቷል ካንተ የተነሳ
አንተ መሀል ገብተህ እኔን አስመለጥከኝ
ውርደቴን ስድቤን ሞቴን ወሰድክልኝ
![](https://i.ytimg.com/vi/n9xHhe6AGms/maxresdefault.jpg)