#abduselam
#ethiopiannasheed
#mezamir
#amharicneshida
#neshida
#abduabera
#selu
#አሊፉን
#መዛሚር
#ዓብዱሰላም
#ነሺዳ
#መንዙማ
#መንሺዳ
#neshida
#abduselam
#mezamir
#selu
#alifun
#menshida
ግጥም - መሀመድ ኢድሪስ ካሳ
ዜማ - ዓብዱሰላም
መዛሚር ነሺድ
የወንጀልን ክምር ከስሩ ገንድሶ
ሀለት የሚያቀና ቀልብ ኣቅልን ኣድሶ
ወንጀል የሚጠርገው በሓሰና ክሶ
ሓያት የሚሞሽር በኣዘል ሰርጎ
ስሙ ሚጣፍጠው እንደማር እንደርጎ
ጀማል ያሸከመው በጀላል ሞሽሮ
ባኽላቅ የዘየነው በራህመት ኣዝምሮ
ሆድ የሚያላውሰው በሸውቁ ሸምሮ
በኑር ፈትል ሰፍቶ በሀይባ ጌጥ ድሮ
እሱን ሳያወሱ መች ይቀናል ኑሮ
በሰማዩ ወለል ቡራቅ ያስጋለበው
ከሩሁ ጧት ማታ ሒክማ ሚታለበው
ስሙ የሚያበርደው የዞላም ትኩሳት
በኣንድ ኣስር የሚያስገኝ ልቅናውን ማንሳት
የኑር ፍሬ ይቀልባል
ኣንቱን ማውሳት ነፍስ ያጠግባል
ልብ ያክማል ጅስም ያጸናል
[Chorus]
ሰሉ ኣለል ሀቢብ መዳኒት ቀለቤ
ሰሉ ኣለል ሀቢብ መድመቂያዬ ጌጤ
ሰሉ ኣለል ሀቢብ ልቅና ሹመቴ
ሰሉ አለል ሀቢብ የዱንያ ንብረቴ
" የኣኼራ ክብረቴ
ሰሉ ኣለል ሀቢብ ክብሬ ነው የሱ ስም
" ሕመም የሚያከስም
"
Verse 2
የሰኪና ቀሚስ ልቤን የሚያለብሳት
ሀጃ የሚሞላው የሱን ዝና ማውሳት
ቀልብን የሚነቅለው ከመእስያ እሳት
ወደኢማን ሓገር ጭኖ የሚያሳፍረው
ወደጀነት ደጃፍ ወስዶ የሚያጋፍረው
የልብን ስብራት ኣሽቶ የሚያቀናው
በኣላህ ጸዳል መንገድ ነፍስን የሚያጸናው
ረህማን ከስሙ ስሙን ያስከተለው
በሪሳላው ቀለም ከውኑን የሚኩለው
ጅስሙ የጠረቃው በኑሩ ወዝ ታሽቶ
ኸልቁን የሚያውደው የልቅናው ሽቶ
እንዴት ልብ ይጸናል ከሱ ፈለግ ሸሽቶ
በምንዳ ሚተካው ኣስር ወንጀል ፍቆ
ኣይሽ የሚዘይነው በኑር ባህር ዘፍቆ
በሲራጥ ኣቀበት ብርሃን የሚያውሰው
መሻት የሚሞላ ወንጀል የሚያብሰው
[Pre Chorus]
ኣንቱን ማንሳት ሩህ ያክማል
በኢማን ወዝ ይሸልማል
በሂዳያ ይከምላል
[Bridge]
በልቅና ከትቦ ስሙን ያደመቀው
በጀሊል ተመርጦ ሒክማው የረቀቀው
መጨረሻ መጥቶ ከፊቱም የላቀው
ተነግሮ ተዘክሮ ሲፋው የማያልቀው
የዳዒሙ ሹሙ
የከውኑ ቀለሙ
የኡመት ጠበቃ
የበድር ጨረቃ
Ещё видео!