ፌቨን በየነ - ትልቅ ነህ | | Feven Beyene - Tilek Neh | New Ethiopian Gospel Song 2020 / 2012
በነገሮቻችን ላይ የእግዚአብሔርን ትልቅነት እናውጃለን።
አንዳንድ ሁኔታዎች እግዚአብሔር የሌለ እስኪመስለን ድረስ በውስጣችን ጥያቄዎችን ይጭሩብናል፤ ነገር ግን እውነታው ይህ አይደለም ፣ በምንም አይነት ቦታ ላይ ብንሆን፣ ሁኔታዎች ምንም ይህል ቢጠነክሩ፤ እግዚአብሔር ሁሌም ታላቅ ነዉ። የኛ ሁኔታ የእርሱን ታላቅነት አይወስንም።
“እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።” — ኢዮብ 36፥26
Some situations in our life might make us feel as if God is not in control, they make us question about the greatness of God. But here is the truth everyone, no matter where we are, no matter how our situations get tough, God is always great and he always remains the same. Our situations don't define the greatness of God!!
“Behold, God is great, and we know him not, neither can the number of his years be searched out.” — Job 36፥26 (KJV)
Click here to get more videos
YouTube: [ Ссылка ]
Follow Me on
Instagram: [ Ссылка ]
Facebook: [ Ссылка ]
በማለዳ ሩጫ በዝቶ
ድካም ዝለት ተንሰራፍቶ
የጀመርነው መንገድ ቢርቅ
ጀንበር ቀድማን ብትጠልቅ
የኛ ሁኔታ ፍጹም - አንተን አይመዝንህም
ትልቅ ትልቅ ከማለት - ከቶ አያግደንም
አንተ ትልቅ ትልቅ ትልቅ ነህ
ከሁኔታ በላይ ትልቅ ነህ
ከነገሮች በላይ ትልቅ ነህ
ጌታ ትልቅ ትልቅ ትልቅ ነህ
ረሃብ ችግሩ ቢያይልም
ሥጋችን ደክሞን ብንዝልም
የመጣው ሕመም ቢከፋ
መሄጃው መንገድ ቢጠፋ
የምናልፍበት መንገድ - በጥያቄ ቢሞላ
የጠላት ድምፅ ቢጮህም - ሊስበን ወደኋላ
በምንም ሁኔታ ውስጥ- እግዚአብሔር ላትተወን
በእጆችህ እንደያዝከን- የነገርከን ቃል አለን
አንተ ትልቅ ኃያል ግሩም ነህ
ከሁኔታ ሁሉ ታልፋለህ
ከነገሮች በላይ ታላቅ ነህ
ጌታ ሆይ ዘላለም ትልቅ ነህ
እግዚአብሔር ሆይ ትልቅነትህን
ተረድተን እኛም አንጨርሰውም
ከትናንትና ዛሬም እስከ ለዘለዓለም
ትልቅነትህን አውቀን ከቶ አንጨርሰውም
በአለማት ሁሉ ፊደል ለቃላት በቀረፅነው
አውቀናል ትልቅነትህን ችለን እንደማንገልጸው፡
#new_amharic_mezmur #new_ethiopian_gosple_song #new_protestant_mezmur
![](https://i.ytimg.com/vi/wFXSnaJrOW4/maxresdefault.jpg)